Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተዘረዘሩት ከሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ግዜ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመንግሥት በሥራ ሰዓት ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ ረዳት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። ከተለያዩ ሕጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት
3. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንከ በተረጋገጠ ሲፒዮ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
የተጫራቾች መመሪያ
- ሎት 1ደንብ ልብስ፡- 10000 (አስር ሺ ብር)
- ሎት 2.የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች–10000 (አስር ሺ)
- ሎት3. ሕትመት 10000 ( አስር ሺ ብር)
- ሎት 4 መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት–10000 (አስር ሺ)
- ሎት 5. ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ……30000 (ሰላሳ ሺ ብር)
- ሎት6. የፅዳት እቃዎች —-10000( አስር ሺ ብር)
- ሎት7.የእንጨትና የብረት ውጤቶች…. 10000 ( አስር ሺ)
- ሎት8.የጥገና ሥራዎች 20000 ( ሃያ ሺ)
የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከጤና ጣቢያው በገዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁሉንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ፈጽሞ ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም።
1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላ ና ጠቅላላ ዋጋ ማሳየት አለባቸው። የሚሞሉት የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
2. ተጫራቾቾ ያቀረቡት ቃሚ ዕቃ ከሆነ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
3. 1. ቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናሱ እና ሲፒዮ በአንድ ፖስታ በማሸግ፣ ፋይናሻል ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ፤ በማሸግ እነዚህን ኦርጅናል የሚል ጽሑፍ መጻፍ።
2. ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ እና ፋይናሻል ሰነድ ኮፒ በአንድ ፖስታ፤ በማሸግ እነዚህን ኮፒ ጽሑፍ የሚል መጻፍ
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያዳንዱ ገጽ ላይ እና በየደረጃው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የበላይ ኃላፊ ፊርማና ስም እንዲሁም ሕጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1- 4 በተዘረዘረ መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር) የሥራ ቀናት በመንግሥት የሥራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ና በጤና ጣቢያው የግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 414 በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታ ሣጥንኑ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።
6. በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60/ስላሳ/ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
7. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት የማጭበርበር (የሙስና) ተግባር ሲፈጽሙ ቢገኙ ወይም ለመፈጸም ቢሞከሩ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገው ተፈፃሚ ይሆናል።
8. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዕቃ የሚመለስ ናሙና ከጨረታው መክፍቻ ቀነ በፊት ለጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ከፍል በአደራ ማስረከብ አለባቸው።
9. ናሙና ሲያመጡ (ሲያቀርቡ) የድርጀቱ ማህተም መደረገ የለበትም፤ ነገር ግን ምልክት አድርጎ ያቀረበ አቅራቢ የመጣው ናሙና ተቀባይነት የለውም።
10.ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናሪው ተጫራች ውል እስኪገባ ድረስ ተመላሽ አይሆንም።
11.ተጫራቾች የሚወዳደሩት በመጀመሪያ በዕቃ ጥራት ሲሆን በሁለተኛው ደረጃ የሚያቀርቡት ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ሆኖ ሁለት ተጫራቾች እኩል ነጥብ ቢያመጡ የግዥ መመሪያና ደንቡ ተፈጻሚ ይሆናል።
12. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 % (አስር በመቶ) በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /C.PO / ሲፒዮ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
13. ውል ሲፈጽምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጪ ምንም አይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም።
14. አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጽምላቸው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ዕቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክቡና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ነው።
15. በግዥ አፈጻጸሙ ላይ በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የቴክኒክ ግምገማ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 7/ሰባት/ የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታ ላወጣው የመንግሥት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል። ነገር ግን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም።
16. መሥሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባው የግዥ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20 % (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
17.ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-43-58- 44-44 ቁጥር 407 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
19. ከጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈው መምጣት ያለባቸው ከአደራጃቸው የጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ተፈርሞ መቅረብ አለባቸው። ነገርግን በቡድን መሪ ተፈርሞ የሚመጣ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም።
- ጥቃቅን አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት (ዕቃ) ብቻ መሆኑን አውቀው የአምራች (አቅራቢ) የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉይህ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
- ነገር ግን በማያመርቱት ምርት (ዕቃ) መወዳደር የሚችሉት እንደማንኛውም ተጫራች ሲፒዮ በማቅረብ (ማስያዝ) አለባቸው።
ጥብቅ ማሳሳቢያ፡-
- መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የሚወዳደሩ አቅራቢዎች፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥፕር ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የሚወዳደሩ አቅራቢዎች፦ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አይገደዱም።
- የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ cpo (ሲፒዮ) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለምሳሌ ቢድ ቦንድና የባንክ ጋራንቲ ቢቀርብ በምንም ተቀባይነት እንደማይኖረው በትህትና እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ