Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የጨረታ ቁጥር 001
የጨረታ ማስታወቂያ
በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የደንብ ልብስ ፣
- ህትመት ፣
- የጽዳትዕቃ፣
- የህክመና እቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ልዩ ልዩ እቃዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና ጀነኔተር ሰርቪስ ።
- ውሃ እና ቆሎ የህንፃ ጥገናዎችን ከአቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድፈቃድያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን እንዲሁም የአቅራቢነት ዝዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና በእስፔስፊኬሽን መሰረት እና በእጃቸው ላይ የሚገኝ እንዲሁም በተጠየቁ ሰአት ወዲያው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው ::
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው ሙሉዝርዝር ሁኔታ የጨረታው መመሪያ ሆኖ ችግሮች ካጋጠሙ በግዥው መመሪያ የሚዳኙ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ሰነድ በፖስታ አሽገው ኦርጅናልእና ፎቶኮፒብለው በመፃፍ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የውል ማስከበሪያ የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 10% ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የወሰዱትን ሰነድ ዋናዋና ቦታዎች ላይ በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም በመምታት ሙሉ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ አለባቸው ፡፡
- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ –
- የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆንና በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 42 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አስር የስራ ቀናት ተከታታይ ቢሮ ቁጥር 412 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የህክምና እቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ከ FDA ሰርተፍኬት ማያያዝ አለባችሁ፡፡
- የጨረታማስከበሪያ (CPO)መቅረብ ስላለበት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት እንድታሲዙ እያሳሰብን፤ በየሎቱ በዝርዝር እንደሚከተለው አስቀምጠናል፡፡
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጭነት ትራንስፖርት ላይ የምትወዳደሩ ሲንግል ፒካፕ የሆነ የታደሰ ቴክኒክ ምርመራ ያደረገ እና ንግድ ፍቃድ ሌብሬ እና ቦሎ እንዲሁም ስሪታቸው እ.ኤ.አ 2000 ጀምሮ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡
- በውሃ እና ቆሎ አቅርቦት ላይ የምትወዳደሩ ያለፋችሁበትን ተቋሙ በፈለገ ሰአት እንደ አስፈላጊነቱ አምጡ ስትባሉ ለአንድ አመት ያክል ማቅረብ አለባችሁ
በመሆኑም
- 6211– ደንብ ልብስ የሚወዳደር = 90,000 ብር
- 6212 – አላቂ የቢሮ እቃዎች የሚወዳደር =36,000.00 ብር
- 6213 – ህትመት የሚወዳደር = 46,000.00 ብር
- 6214- የህክምና እቃዎች የሚወዳደር = 60,000.00 ብር
- 6218 – አላቂ የጽዳት እቃዎች የሚወዳደር = 80,000.00 ብር
- 6219 – ልዩ ልዩ እቃዎች የሚወዳደር 60,000.00 ብር
- 6313 – ቋሚ እቃዎች የሚወዳደር = 100,000.00 ብር
- 6243 የኤልክትሮኒክስ ጥገና እና ጀነሬተር ሰርቪስ ላይ የሚወዳደር = 38,000.00 ብር
- 6244 የህንፃ ጥገና ላይ የሚወዳደር = 38,000.00 ብር
- 6255 የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚወዳደር = 14,000 ብር
- 6419 የውሃ እና ቆሎ ቅርቦት ላይ የሚወዳደር = 14,000 ብር
- አድራሻ ፤– አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፤– በስልክ ቁጥር 011-439-89-08
ከላይ ጨረታ የወጡ መደቦች ላይ ዋጋ የሚሞላ ተጫራች የሞላውን እቃ ድምር ሁሉም ላይ የሞላ ተወዳደሪ የሁሉንም ድምር የጨረታ ማስከበሪያ ማሳያዝ አለበት፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ