Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 100/4/3612/001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በመጀመሪያ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት፣ ማስጠገን እና ማሠራት ይፈልጋል።
- ሎት-1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት-2. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-3. የደንብ ልብስ
- ሎት-4. የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች
- ሎት-5. ለጥገና የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት-6. አላቂ የሕክምና ዕቃዎች
- ሎት-7 ቋሚ መገልገያ ዕቃዎች እና መሣሪያዎች
- ሎት-8. የኮፒ ማሽን፣ ላፕቶፕ እና ኮምፒውተሮች የጥገና ሥራዎች
- ሎት-9. ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት-10. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች መሣሪያዎች እና አጋዥ መጽሐፎቶች
- ሎት-11. የጭነት አገልግሎት ግዥ እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት
- ሎት-12, የሠራተኞች ሻይ ክበብ
ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች በመንግሥት ግዥ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ (Tax clerance) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዝጋቢነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ በመንግሥት ጨረታ ግዥ ላይ ለመሳተፍ በፋይናንስ ቢሮ ያልታገዱ።
2. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ የአቅራቢዎች ምዝገባ (www.egp.ppa.gov.et) ላይ ተመዝግቦ (Supplier List) ውስጥ የተካተቱ እና ስለመመዝገባቹ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ት/ቤቱ በonline ያረጋግጣል።
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-11:30 ሠዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር ብቻ /ሁለት መቶ ብር/ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 በመከፈል ከግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር R-18 ደግሞ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ሥር በተቀመጠው ዝርዝር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስም በማሠራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ተጫራቾች መረጃቸውን በአራት ካኪ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) በማድረግ ፋይናሻል ኦርጅናል፣ቴክኒካል ኦርጅናል እና የፋይናሻልና የቴክኒካልን ለየብቻው ኮፒ (ቅጅ) ብሎ በመለየት እንዲሁም (CPO) ለብቻ በትንሹ ፖስታ በማሸግ ከዋናው (original) ቴክኒክ ሰነድ ጋር አያይዛችሁ በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
|
ሎት |
የዕቃው /የሥራው/ ዓይነት |
ከአጠቃላይ በጀት የተወሰደው መጠን በ% |
ለየሎቱ የሚያስይዙት ማስከበሪያ (CPO) መጠን |
|
1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
0.5% |
11,750.00 ብር |
|
2 |
የጽዳት ዕቃዎች |
0.5% |
10,000.00 ብር |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
0.5% |
9,500.00 ብር |
|
4 |
የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች |
0.5% |
1,000.00 ብር |
|
5 |
ለጥገና የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች |
0.5% |
5,500.00 ብር |
|
6 |
አላቂ የሕክምና እቃዎች |
0.5% |
400.00 ብር |
|
7 |
ቋሚ መገልገያ ዕቃዎች እና መሣሪያዎች |
0.5% |
11,500.00 ብር |
|
8 |
የኮፒ ማሽን፣ላፕቶፕ እና ኮምፒውተሮች የጥገና ሥራዎች |
0.5% |
1,820.00 ብር |
|
9 |
ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች |
0.5% |
1,435.00 ብር |
|
10 |
አጋዥ መጽሐፎች |
0.5% |
500.00 ብር |
|
11 |
የጭነት አገልግሎት ግዥ እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት |
0.5% |
500.00 ብር |
|
12 |
የሠራተኞች ሻይ ከበብ |
0.5% |
7,500.00 ብር |
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ /specification/ ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ በየገፁ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ ግዴታ ነው።
6. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የራሳችሁን እሴት ያልጨመራችሁ እና አምራች ያልሆናችሁ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ 200.00 ብር ብቻ /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ሲፒኦ በማስያዝ መወዳደር ትችላላችሁ አምራች የሆናችሁ ከአደራጃችሁ ተቋም የትምህርት ቤታችንን ስም እና የጨረታውን ቁጥር ጠቅሰው በመጻፍ መሳተፍ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ (CPO) 10% ያስይዛሉ፤ እንዲሁም አታችመንት ደረሰኝ QR ኮድ ያለው መሆን ይኖርበታል።
8. የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን 04፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያግደውም እንዲሁም የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው /ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሀገር አቀፍ ክብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ላይ ናሙናዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
10. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መለኩ በድጋሚ ተጽፎ መፈረም ይኖርበታል።
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብና ንብረት ክፍል የማስረከብ ግዴታ አለበት።
12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ተጫራቾቹ ያቀረቡት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታ ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ለ60 የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል።
14. አቅራቢው (አሸናፊ) ድርጅቶች ከግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ጋር ውል ከገባችሁ ጊዜ ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉችሁትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች አጠናቀው ባያስረክቡ ለዘገዩበት ጊዜ መጠን ላይ 10% (አስር በመቶ) ሳይበልጥ በየቀኑ 0.1% (አንድ በመቶ) የጉዳት ካሳ ይቀነሳል።
15. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ሎት 11 የጭነት አገልግሎት በተመለከተ ከላይ በተራ ቁጥር ከተዘረዘሩት መስፈርት በተጨማሪ የተሟላ የባለቤትነት ማረጋጫ ሊብሬ፤ የሶስተኛ መድን፤ ኢንሹራንስ፤ ቦሎ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለበት።
17. ሎት 8ን በተመለከተ ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡትለሥራዎቹ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን እና አጠቃላይ የጉልበት ዋጋን ጨምሮ ነው እንዲሁም ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት ሥራዎቹን በአካል በመቅረብ መመልከት ግዴታ ሆኖ ማየታቸውን የሚያረጋግጥ ፊርማ ማኖር ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡– በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት ፅ/ ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር የአንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት አስኮ ሊዝ መንደር ቆዳ ሜዳ አጠገብ ይገኛል (የቀድሞ ረታ ት/ቤት) ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁጥር 011-2-73-14-41 ወይም 011-2-73-08-02 ወይም 011-73-19-38
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር
አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት