Addis Zemen (Oct 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ለገርቢበር ማዘጋጃ ቤት በ2019 በጀት ዓመት የማዘጋጃ ቤቱን ዙሪያውን ማሳጠር እና መጸዳጃ ቤት፣ የጥበቃ ቤት ለማስገንባት ስለተፈለገ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ደረጃቸው G.C-9/B.C-9 እና ከዛ በላይ የሆኑ ፡-
- የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈሉ (የታደሰ ንግድ ምዝገባ)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት
- የንግድ ምዝገባ ስራ ፍቃድ
- የTIN የምዝገባ ሰርተፍኬት
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት
- የጨረታ ዋስትና 50000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ ፧
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-
በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሺያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ከ21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ — ስልክ ቁጥር 0925 109 200 0929 947 257 0929 938 904 0939 330 829 0916 515 263
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ ስልጢ ወረዳ