የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 22, 2026)

የአስረኛ ዙር የበድሪ በሪ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት
የጨረታ ማስታወቂያ
በከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ – ሠ) መሠረት የወጣ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን፤ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከተራ ፊደል (ሀ) እስከ (ሠ) በተዘረዘረው መሠረት፣ በሐረሪ ከተማ ጀጎል በድሪ በሪ አካባቢ በሚባል ቦታ ለመኖሪያ በአስራ አንድ (11) ብሎኮች የተዘጋጁ ስልሳ ሦስት (63) ፓርስሎች፤ እና ለንግድ መደብሮች የሚውሉ በስድስት (6) ብሎኮች ሰላሳ አንድ (31) ፓርስሎች፤ እንዲሁም አንድ (1) ለካፌ ንግድ አገልግሎት የሚውል በጠቅላላው ዘጠና አምስት (95) ፓርስሎች የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የይዞታው አገልግሎት (Land Use)

 

የብሎክ ብዛት (Blocks)

 

የፓርሰል ብዛት (Parcels)

 

ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ (Residential)

 

11 ብሎኮች

 

63 ፓርስሎች

 

ለንግድ መደብሮች የሚውሉ (Commercial)

 

6 ብሎኮች

 

31 ፓርስሎች

 

ለካፌ ንግድ አገልግሎት የሚውል (Caf )

 

—-

1 ፓርሰል

 

ጠቅላላ ድምር (Total Allocation)

 

17 ብሎኮች

 

95 ፓርስሎች

 

የተጫራቾች መመሪያ እና የመወዳደሪያ መስፈርቶች

  1. የሰነድ ሽያጭ፦ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላል። ከፍያውን በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባዘጋጀው የኦንላይን ፖርታል (Harari Land Lease Tender Portal) በድረ-ገፅ https://sltms.hararsmartlandsystem.gov.et በመግባት ማከናወን ይቻላል። ለዚህም 1,500 ብሩን በሐረር ከተማ በሚገኝ ማንኛውም ባንክ ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ በተዘጋጀው አካውንት ቁጥር 1000017606364 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኦንላይን ፖርታሉ ላይ ስካን አድርጎ በማያያዝ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  2. አማራጭ የሰነድ ግዢ አገልግሎት፦ የኦንላይን ፖርታላችንን አጠቃቀም ለሚቸገሩ ተጫራቾች አማራጭ የግዢ ማዕከላትን ያዘጋጀን ሲሆን፤ ተጫራቾች በአካል በመቅረብ በመሶብ 1 ማዕከል እንዲሁም በዋናው መሥሪያ ቤታችን ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር 49 በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በቀላሉ መግዛት ይችላሉ።
  3. የሰነድ ማስገቢያ ጊዜና የመጨረሻ ቀን፦ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል። ለቦታዎች በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ መወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት፣ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የሰነድ ማስገቢያው የመጨረሻ ጊዜ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
  4. የሳጥን መዝጋትና መክፈቻ፦ የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ፤ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አራተኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO)፦ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5% (አምስት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (በCPO ብቻ) በጥቅሉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. የቅድመ ክፍያ መጠን፦ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ከ20% (ከሃያ ፐርሰንት) ማነስ የለበትም፡፡
  7.  የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ፦ የተጫራቾች አሸናፊነት የሚለየው ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80% (ሰማንያ ፐርሰንት) እና የቅድመ ክፍያ መጠን 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጥምር ውጤት ተሰልቶ በሚገኘው ከፍተኛ ነጥብ መሠረት ይሆናል።
  8. የCPO ተመላሽ፦ የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጹ በኋላ፣ በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. ለተጨማሪ መረጃ፦ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://hudco.gov.et  በመግባት ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
  10. ማሳሰቢያ፦ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *