በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል እቃዎች ግዥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል እቃዎች ግዥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 24, 2026)

የአገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል

  1. የጽዳት እቃዎች (በሎት)
  2. የደንብ ልብስ (በሎት)
  3. ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (በነጠላ)
  4. የተሸከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይ (በነጠላ)
  5. የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ (በነጠላ)
  6. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች (በነጠላ)
  7. ሃንድ ኮምፓስተር (በነጠላ)

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
  2.  አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ ወይም የታደሠ የንግድ ስራ ፈቃድ
  3.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  4.  የግዥ መጠን ከብር 500,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንን፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች በግብር አመቱ ተገቢውን የታከስና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1–5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችና አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% ከነቫቱ ከታወቀ  ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከእነዚህ ውጭ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9.  የመጫረቻ ሰነዱ የጨረታ ሰነዱ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ45 ቀን አርባ አምስት ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  10. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/ መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራቾች ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ የሌለው ወይም የጨረታ ማስከበሪያው የሚያንስ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  14. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችሉት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን ከውድድር ውጭ የሚደርግ ይሆናል።
  15. በጨረታ በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  16. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኝም በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ/አገልግሎት ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት እንደአስፈላጊነቴም በደሴ ከተማ የአስተዳደር ክልል ውስጥ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ በራሱ ማጓጓዥ ማስጫኛ እና ማውረጃ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  18. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው ለጽዳት እቃና ለደንብ ልብስ በሎት ሲሆን ከእነዚህ ውጭ ያሉትን በነጠላ ዋጋ ውድድር ይሆናል፡፡
  19. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም

በስልክ ቁጥር 033 312 91 22/ 033 311 10 41/1048/ 10 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡

አድራሻ ፡– ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት