Addis Zemen (Oct 24, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዢ
ድርጅታችን ዘድረ የገበያ ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶቹን በውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ እና ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የኦዲት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. የፌዴራል ታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው
3. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ(AABE) የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. የግብር እዳ የሌለባቸው መሆኑን የሚገልፅ ወቅታዊ የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ
የማመልከቻ ሁኔታ
መስፈርቱን የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች የቴክኒክ (Technical) እና የፋይናንስ(Financial) ሰነዶቻችሁን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድታስገቡ እንጋብዛለን፡፡
አድራሻ፡– ከአውቶብስ ተራ ወደ ሰባተኛ መሄጃ ቤተል/ አለምባንክ ታክሲ መጫኛ ዘድረ የገበያ ማዕከል 2ኛ ፎቅ ዋና ቢሮ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0964 454 647 / 0905 300 300
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘድረ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር