በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ ቤት ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ በተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ ቤት ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ በተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 25, 2026)

የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

  1. የጨረታው ዙር 19ኛ
  2. የጨረታው አይነት መደበኛ
  3. የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ ይህንኑ አዋጅ በማስፈጸም የአብክመ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለማያዝ በወጣው ደንብ ቁጥር 03/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10  በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ “ሀ እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ በተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታው ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሸ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች ሁለት የተለያየ ፖስታዎችን በማዘጋጀት ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውስጥ በመለየት ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሦስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን እንዲሁም ሰርአን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን በብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በሰም ወይም በአካባቢው በሚገኝ ማጣበቂያ በማሸግ እና ፖስታዎቹ . ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15/2/19ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው አስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ማለትም 27 /2/19 በከተማ አስተዳደሩ ለጨረታ ተግባር በተዘጋጀው ቦታ ኦርጂናሉን ሰነድ በዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እና ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 30/02/2019 ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን 27/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።
  7. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  8. ጨረታው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት የሸ ከ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 30/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በጽ/ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ አንዲሁም የሸ/ ከ/ አስ/መሬት ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች የጨረቻ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመኖሪያ የመነሻ ዋጋውን በካሬ ተባዝቶ 80 ፐርሰንት ማነስ የለበትም።
  12. ተጫራቾች የጨረቻ ማስከበሪያ ሲፒአ ለድርጅት የመነሻ ዋጋውን በካሬ ተባዝቶ 5 ፐርሰንት ማነስ የለበትም።

ማሳሰቢያ፡– በግልጽ የማይነበቡ ስርዝ ድልዝ ያለባቸው ሰነዶች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ

በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *