አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአውቶቡስ ዲስፕሌይ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአውቶቡስ ዲስፕሌይ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 25, 2026)

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/023/2019 የአውቶቡስ ዲስፕሌይ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ–ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ስታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክቁጥር : 011 666 3206

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *