በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 27, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር መከ/ሰ/ምስ/ዕዝ/ግ/ጨ/01/2019

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የጀኔሬተር መለዋወጫ፣ የዳቦ ማሽን መለዋወጫ፣ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና አላቂ የጋራዥ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች፡–

1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ–ሥርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ባወጣው የመንግሥት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የተሟሉና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።

4. ተጫራቾች ተ.ቁ 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ከጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ፋይናንሻልና ቴክኒካል እንዲሁም ኦርጅናልና ኮፒ ማስታወቂያው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

6. ለተጨማሪ ማብራሪያና ሰነድ ማስገቢያ፡–

ሀ/ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ፡– ዘወትር በሥራ ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሠመራ ከተማ የሰሜን ምስ ዕዝ/ፋይ ሥራ አመራር ግዥ ክፍል ቢሮ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡– 0991 454 479 / 0939 055 793 መጠየቅ ይችላሉ።

ለ/ የሰነዱ ሽያጭ የሚከናወንበት አድራሻ፡– በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡

ሐ/ ጨረታው የሚላክበት አድራሻ፡– በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ።

መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡– በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡

ሠ/ ንብረቱ ገቢ የሚሆነው፡– ሠመራ ከተማ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ንብረት ግ/ቤት ነው።

. ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ