Addis Zemen (Oct 27, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም
- ሎት 1 የአልትራ ሳውንድ ባለሙያ
- ሎት 2 የካፍቴሪያ አገልግሎት ጨረታ ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ለካፍቴሪያ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ።
- አገልግሎቱን ለማቅረብ የሚያስችሉ መሰረታዊ ዕቃዎችን ማቀዝቀዣ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበሮችና ጠረጴዛ፣ ቴሌቪዥን፣ ማብሰያ ዕቃዎች፣ ወዘተ…/ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ወይም 3% ተጠቃሚዎች እና ከገቢዎች በልዩ ሁኔታ ለሠራተኞች ለምሳ ድጎማ ማቅረብ እንዲችሉ ደብዳቤ ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ መጫረት ይችላሉ።
- ተጨማሪ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል።
- የውሃ እና የመብራት ፋጆታ በመሥሪያ ቤቱ የሚሸፈን መሆኑንን አውቃችሁ ለሠራተኛው የምትሞሉትን የምግብ፣ የለስላሳና የሻይ ቡና ዋጋ ላይ በአነሰተኛ ዋጋ እና በጥራት እንደምትሠሩ ማወቅ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርገው ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩት በአነስተኛ ዋጋ ድምር ስለሆነ እያንዳንዱን የምግብና የለስላሳ፣ የሻይ ቡና ዋጋ መሙላት አለባቸው። የሁሉም ጠቅላላ ዋጋ ድምር አነስተኛ የሆነ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።
- እያንዳንዱ ዝርዝር ላይ ዋጋ አለመሙላት ከውድድር ውጪ ያደርጋል።
- ለአልትራሳውንድ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በራዲዮሌጂ ቴክኖሎጅ የተመረቀ/ች ዲግሪ ያለው።
- በሙያው ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ የአልትራሳውንድ ሥራ ልምድ ያለው/ያላት።
- የታደሰ የሙያ ፍቃድ ያለውና እና በዘርፉ የተሰማሩበትን ንግድ ፋቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ማቅረብ የሚችሉ።
- ባለሙያው የሠራቸውን ውጤት ሲስተም ላይ ማስገባት ግዴታ አለበት።
- ጠቅላላ የአገልግሎቱ ዋጋ ከ10000/አስር ሺህ ብር በላይ ከሆነ ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚቆረጥ ይሆናል።
- በሳምንት ለሶስት/3/ ሙሉ የሥራ ሰአት ወይም ሰኞ፣ ማክሰኞ እና እሮብ መሥራት የሚችሉ እና በሳምንት አምስት /5/ ቀን ማለትም ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ እና አርብ መሥራት የሚችሉ ሰነዱን ለይተው መውሰድ ይችላሉ።
- የአገልግሎት ክፍያው ከተሰበሰበው ገቢ ላይ ለተቋሙ 50 ፐርሰንት እና ለባለሙያው 50 ፐርሰንት መሆን አለበት።
- የጨረታ መስፈርቱን እኩል ተወዳድረው ላመጡ ተወዳዳሪዎች መ/ቤቱ ፈተና አውጥቶ አወዳድሮ አሸናፊውን ይለያል።
ለሁለቱም ጨረታ የሚያገለግሉ መስፈርቶች
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋዉም በ10ኛዉ ቀን 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ ጨረታዉ በግልጽ የሚከፈተው በ11ኛው (በአስራአንደኛው) ቀንከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት አገልግሎቶች
- ሎት1-5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ/
- ሎት-2-13000/አስራ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111546900/011 54 60 29/0111 26 80 48 / 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡– ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ሕንፃ ፊት ለፊት
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ