Addis Zemen (Oct 26, 2026)
ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው በሥራ ላይ የሚገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ለማወዳደር
የወጣ ማስታወቂያ
እህቶቼ የሴቶች ደህንነት ማህበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 እና በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ ለሆኑ ሴቶችና ህፃናት የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችንና ድጋፎችን በመስጠት፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የድህነት ችግር ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
ስለሆነም ማህበሩ የዓመቱን ሂሳብ ለማስመርመር ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው በሥራ ላይ የሚገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በማወዳደር ለመምረጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁና በሥራ ላይ የምትገኙ የኦዲት በሥራ ላይ የምትገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12 (አሥራ ሁለት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያስፈልጉትን የሙያ ማረጋገጫና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎች (የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ መረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ) በማሟላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአካል በማቅረብ በውድድሩ እንድትሳተፉ በዚህ ማስታወቂያ ጥሪ ያቀርባል።
አድራሻ፡- መካኒሳ አቦ መስማት ከተሳናቸዉ ት/ቤት ጀርባ 500 ሜ ገባ ብሎ
ስል: 011 372 4760, 091 125 0601
ኢሜል፡ mysisterswwa@hotmail.com
እህቶቼ የሴቶች ደኅንነት ማኅበር