Be'kur (Oct 26, 2026)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የማገዶ እንጨት ፣
- ሎት 2.የዳቦ አቅርቦት፣
- ሎት 3.የምግብ ምርቶች ፣
- ሎት4. የእህል ምርት ውጤቶች እና
- ሎት 5. የኤሌክትሪክ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላ ላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስና ግብር ግዴታን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ታክስ ክሊራንስ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000 (አስር ሺ ብር) በላይ ሶስት በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶየሚቀር ይሆናል፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፤የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ ቲን ፣የታክስ ክሊራንስ፣ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ 1 በመክፍል ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከጥቅምት 16/2019 ዓ.ም.ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓላት ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ወይም ኮሬክሽ ፍሉድ መጠቀም አይፈቀድም፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃዉን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ እና የጫኝ አውራጅን ወጭ ታሳቢ በማድረግ መወዳደር ሲሆን በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- አድራሻ ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80/09 20 50 68 87/09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት