Addis Zemen (Oct 26, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ለመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ቧንቧ ና መገጣጠሚያ፣ የውሃ ቆጣሪዎች ፣ የውሃ ቧንቧ መሳሪያ ዕቃዎች (Tools)፣ የኤሌክትሪክ ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች (Laboratory) ፓምፕ/Pump ኮምፒውተር ፕሪንተር፣ ቢል ፕሪንተር፣ የቢሮ ወንበሮች /Furniture የባጃጅ ስፔር ፓርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀዉን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደስ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ግብር የከፈሉ።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN – Number) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የአቀራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም መሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
5. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ላልቀረበና ማንኛውንም ስህተት ቢፈፅም ኃላፊነቱ የተጫራቹ የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል።
6. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል። እንዲሁም የመቂ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት።
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማሰከበሪያ በየሎቱ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) የCPO ቼክ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኋላ በገበያ ጥናት አሸናፊው ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚሰጥ ዋጋ ይሆናል።
9. አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃውን በድርጅቱ መስሪያ ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦርጅናል መሆን ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
12. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ቴክኒክና ፋይናንስ በተናጠል በታሽገ ኢንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
13. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን በ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
14. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10/00 ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
15. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
16. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ዉሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ–
- የሚፈለገው የዕቃ ብዛት የምናሳወቀዉ የማሸነፊያ(የጨረታ) ዋጋ ከተለየ በኋላ መሆኑን እንገልጻለን።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን እና ያለመሆኑን የጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል።
- ለበለጠ መረጃ በ ሞባይል ቁጥር ሞባይል 0912999499 ወይም 0912309452 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፦ የመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የመቂ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት