የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 27, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር አ/ጤ/ጣ 001/2019 ዓ.ም.

  1. ሎት 1 የደንብ ልብስ 
  2. ሎት 2 የጽህፈትና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 
  3. ሎት 3 ሕትመት 
  4. ሎት 4 መድኃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ 
  5. ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች ፣ 
  6. ሎት 6 ልዩ ልዩ፣ 
  7. ሎት 7 የጥገና ዕቃዎች 
  8. ሎት 8 የጭነት አገልግሎት 
  9. ሎት 9 ቋሚ ዕቃዎች

ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ግዥዎች መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

1.ለተጠቀሱት ዕቃዎች ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከአቃቂ ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 510 በአካል በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት ዕቃ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት ምደብ 1  ለሎት 1 የብር 49572(አርባ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሁለት ብር)  2. ለሎት 2 የብር 16000 (አስራ ስድስት ሺህ ብር)፣  3. ለሎት 3 የብር 21006 (ሃያ አንድ ሺህ ስድስት ብር)፣ 4. ለሎት 4 የብር 69012 (ስልሳ ዘጠኝ ሺህ አስራ ሁለት ብር)፣  5. ለሎት 5 የብር 47725 (አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ብር)፣  6. ለሎት 6 የብር 9975 (ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ብር)፣  7. ለሎት 7 የብር 41122 (አርባ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር)፣  8 ሎት 9 የብር 123345 (አንድ መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለትና ተመላሽ የሚሆን ዋስትና ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች በሚወስዱት የመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ቫትን ያካተተ ዋጋ በመሙላት ሙሉ ሠነዱን መመለስ አለበት።

7. በጤና ተቋሙ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን በመሰረዝ ማስተካከል አይቻልም።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም በሠነዱ ላይ በመምታት ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በተለያ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 508 ዘወትር በስራ ሠዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት ) ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

10. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የሚያስዝ ይሆናል።

11. ተጫራቾች በሁሉም በሚጫረቱበት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ 1 (አንድ) ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በእጅ የማይያዙ ናሙናዎችን ግልፅ በሆነ ፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በሚያቀርቧቸው ናሙናዎች ላይ ከአምራች ድርጅቱ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ምልክት ወይም የተጫራቹ ማህተም የተደረገበት ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. በመሥሪያ ቤቱ የቀረቡ ናሙናዎች ግዥዎች ላይ ተጫራቾች ቦታው ላይ በመገኘት ማየት ወይም መለካት ይኖርባቸዋል።

13. የተሰረዘ፣ የተደለዘ እና ግልፅነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ከተቋሙ የድጋፍ ደብዳቤ እና የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

16. ከጥቃቅን አምራቾች ጋር በትስስር ለሚሰሩ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት መጫረት ይችላሉ።

አድራሻ፡- አቃቂ ልዩ ስሙ የድሮው ምክር ቤት

ስልክ ቁጥር 011-842-0330

የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ