Reporter (Oct 28, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተው ተሸከርካሪ ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የተበዳሪው ስም |
የአስያዡ ስም |
የሠሌዳ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የተሰራበት ዘመን |
የንብረቱ ዓይነት |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ |
ሐራጅ የሚከናወንበት |
||
|
ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታው ሰዓት |
||||||||
|
ኢስት ሳይድ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር |
ኢስት ሳይድ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር |
አአ– 03-B57086 |
F––EL |
LSVUB6E46N2019395 |
2022 |
ቮልስዋገን አይ.ዲ4 የኤሌክትሪክ መኪና |
ብር 3,000,000.00 (ሶስት ሚሊዮን) |
ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም |
ጠዋት 3፡00-5:30
|
ጠዋት 5.30-5:50
|
የሐራጅ ደንቦች፡–
- ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- አሸናፊው/ዋ የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው። አሸናፊው/ዋ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው። ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
- ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
- ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ቀረጥም ካለ በሙሉ በጨረታው አሸናፊ/ዋ የሚከፈል/የሚከፍሉ ይሆናል።
- አሸናፊው/ዋ ያሸነፉበት ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
- የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም። ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።
- ባንኩ ተሸከርካሪውን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል።
- የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው።
- ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ተሸከርካሪ መጎብኘት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557 2535 ወይም 09 11 15 24 90 ወይም 09 11 45 62 03 ወይም 09 19 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘመን ባንክ አ.ማ.
Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia