የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 28, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ 001/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም።

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛመጅ ዕቃዎች
  • ሎት 2 የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሉት 3 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4 ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልተው መገኘት አለባቸው።

1. በመስኩ ሆኖ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት ምዘገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው መስኮች ከ2017 ዓ.ም ወዲህ ቢያንስ አንድ ዙር በመንግስት ግዥ ላይ በመሳተፍ በገቡት ውል መሠረት ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያለቸው አይገደዱም።

3. የጽሕፈት መሳሪያዎችን አላቂ ዕቃዎችንና የተለያዩ ቀለሞችን የሚያቀርቡ ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ጨረታው በሚታሸግበት ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ላይ ስለትክክለኛነቱ አረጋግጦ ለመ/ቤቱ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ ጨረታው ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ ማሸጊያ ሰዓት ድረስ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 7 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000454348471 ላይ ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4:30 ሠዓት ላይ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት ሥራ ቀን ይከፈታል።

7. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች በራሱ ወጪ አጓጉዞ ቦንጋ ማዕከል በሚገው ፋይናንስ ቢሮ ዕቃዎችን አስመርምሮ ስለትክክለኛነቱ በማረጋግጥ ማስረከብ አለበት።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር ለሎት 2 ለሎት3 እና ለሎት 4 ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ማቅረብ አለባቸው።

9. ጨረታውን ያሸነፈ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% አስር ፐርሰንት ማስያዝ አለበት

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡ ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ሲያጋጥሙ በስልክ ቁጥር 047 331 188 መጠየቅ ይችላሉ።

የደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *