የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ (የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዣ) በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ (የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዣ) በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 29, 2026)

የደረቅ ጭነት ማመላላሻ ጨረታ ቁጥር 001/2019

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ/ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማራገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ በልግና ለመሐር የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከድርጅቱ ማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልገውን መድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በኩንታል በአንድ ኪ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ህጋዊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ ተቋም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣የተሽካካሪዎቹን ኢንሹራንስ ዋስትና የዘመኑን ማቅረብ የሚችል
  3.  ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን ለመወጣቱ መልካም የሥራ አፈጻጸም ያለውና ቢችል ማቅረብ የሚችል
  4.  የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችልም።
  5.  ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ ዋስትና ሲፒኦ(C PO) 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የተሸከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 1,000 ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሰሌዳ ቁጥር፣የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከመንግስታዊ አካል ወቅታዊ መረጃ የተሰጠና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ይህ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ በመክፈል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ኅ/ሥራ ዩኒየን ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  8. የጨረታው ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።
  9. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያን ቀን ልክ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየን ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከ11ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ለቀጣይ ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ሙዱላ ከተማ መናኸሪያ መግቢያ አስፓልቱን ገባ ብሎ ባለው ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር፦0916838378/0916838348

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *