የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ድርብ ተግባር ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በሐራጅ በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ድርብ ተግባር ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በሐራጅ በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 30, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/11፣ 216/92 እና 97/90 መሠረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው / መያዣ ሰጪው ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የንብረት ዝርዝር /መግለጫ/

የሐራጁ መነሻ ዋጋ ( ብር )

የሐራጁ ደረጃ

የሐራጁ ቀንና ሰዓት

ዲዲጋ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር

ነቀምቴ ከተማ

ድርብ ተግባር ተሽከርካሪ (Toyota Double Cab Vehicle)

  • Model: KUN25L-PRMDHV
  • Chassis: MROFR22G5F0731894

3,375,656.58

1ኛ

ሕዳር 10/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ፡–

1. ከላይ የተመለከተውን ንብረት ለመግዛት ፍላጎትና አቅም ያለው የሐራጅ ተሳታፊ የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25%) የሐራጅ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሐራጁ ቀን ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት በመመዝገብ መሳተፍ ይችላል።

2. ሐራጁ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ይካሄዳል።

3. ለሐራጅ ማስከበሪያ የሚያዘው ገንዘብ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ሐራጁን ላላሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ የሐራጁ አሸናፊ በራሱ ፈቃድ ሐራጁን ከተወው ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሠረዛል።

4. የሐራጁ አሸናፊ መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን ቀረጥ ከፍሎ ወይም ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እና የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ 15 በመቶ (15%) ተ.እ.ታ (VAT) እና ሌሎች በሕጉ መሠረት የሚከፈለውን ማናቸውንም ክፍያ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን በመክፈል ስመ–ንብረቱን ወደ ራሱ ማዛወር አለበት።

5. የሐራጁ አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ አለበት፤ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖና ጨረታው ተሠርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቂያ ይወጣል።

6. ስለንብረቱ ዝርዝር ሁኔታ እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 057-660-7347 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

7. ማንኛውም በሐራጁ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ንብረቱ በሚገኝበት ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት መርሐ–ግብር መሠረት መጎብኘት ይችላል።

8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *