በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 1)፣ የተለያዩ ሞተሮች (ሎት 2) እና የተለያዩ የውሃ ማቴሪያሎችና የግንባታ ግብዓቶች (ሎት 3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 1)፣ የተለያዩ ሞተሮች (ሎት 2) እና የተለያዩ የውሃ ማቴሪያሎችና የግንባታ ግብዓቶች (ሎት 3) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 31, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተሮች እና የተለያዩ የውሃ ማቴሪያሎች (የውሃ መስመር እቃዎች) እና የግንባታ ግብዓቶች እቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም፡–

  1. ሎት1 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች
  2. ሎት2 የተለያዩ ሞተሮች
  3. ሎት2 የተለያዩ የውሃ ማቴሪያሎች (የውሃ መስመር እቃዎች) እና የግንባታ ግብዓቶች

1, በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።

3. በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት 1 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ፣ ለሎት 2 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለሎት 3 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6. ተጫራቾች በእያንዳንዱን ሎት የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶከመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ክ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ።

7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።

8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የመውረስ መብት አለው።

9. ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል። ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ ከ8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

10. ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉለውም።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

13. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

  • ማሳሰቢያ፡– ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው።
  • ጨረታ ሎት 1 እና ሎት 2 ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆኑ ሎት 3 ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን እንገልፃለን።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13-37-12-45/ 09-23-13-37-39 እና 09-23-51-95-14

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት