Reporter (Nov 01, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።
|
ተራቁ.
|
የተበዳሪው ስም
|
አስያዥ
|
አበዳሪው ቅርንጫፍ
|
የተሽከርካሪው አይነት
|
የሰሌዳ ቁጥር
|
የሞተር ቁጥር
|
የሻንሲ ቁጥር
|
የስሪት ዘመን
|
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር (ቫትን ሳይጨምር) |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
ኤልሳቤጥ ባለው ካሳ
|
መላኩ ባለው ካሳ
|
የሺ ደበሌ
|
ሱዙኪ ዲዛየር አውቶሞቢል
|
አአ-02-B82171
|
K12MM4 716628 |
MA3ZF6C1 1MA787034
|
2021 እ.ኤ.አ
|
3,130,434.78
|
ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት
|
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል።
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው። ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
- የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጁ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ እስከ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር የጨረታዉ አሸናፊ (ገዥዉ) ይከፍላል።
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ በስልክ ቁጥር 011 470 6380/ 011 466 6593 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።