Reporter (Nov 01, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፤ ተሸከርካሪዎቹ ተለያይተው አይሸጡም፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለየብቻ መሰራት አለበት።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሸከርካሪው ዓይነት እና የተሰራበት ዘመን |
የተሸከርካሪው ሞዴል |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
|
1. |
አቶ ሄኖክ ሳህሉ ሙሉዓለም |
ተበዳሪው |
ኢት-03-A43364 |
የጭነት ቻይና–ሲኖትራክ፣ እ.ኤ.አ. 2025 |
ZZ1257S4341W |
LZZ5BLSF3 SN297936 |
WP12S400E 2011424 SOS0929 |
15,306,345.00 |
ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም |
4፡30- 5:30 |
5:30-6:00 |
|
2. |
አቶ ሄኖክ ሳህሉ ሙሉዓለም |
ተበዳሪው |
ኢት-03-42534 |
ተሳቢ፣ ቻይና– ሲኖትራክ፣ እ.ኤ.አ. 2025 |
SDSL2210LIAT. |
LA9940Z37 S0LXD156 |
———- |
4,798,746.00 |