አዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 1/2019

አዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ የስፌት ዋጋ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት. 3 አላቂ የትምህረት እቃዎች
  • ሎት 4. የህክምና እቃዎች
  • ሎት 5 ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች
  • ሎት.6 ልዩ ልዩ መጽሀፍት
  • ሎት. 7 ትራንስፖርት
  • ሎት 8 የመስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 9 ለህንጻ ለቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና
  • ሎት 10. ለፕላንት ማሽነሪና መሳሪዎች መግዣ

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራች ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኃል።

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ አለበት

2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ማንኛውም ተወዳዳሪ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ አቅራቢነት ዝርዝር / supplier list/ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

5. በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላላፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

6. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች የምትወዳደሩበትን እቃ የራሳችሁ ምርት /አምራች/ መሆናችሁን የሚገልጽና በአመረታችሁት እቃ ላይ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳዉቃለን።

7. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ/ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ክፍል ከ2:30-11:30 ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8. የጨረታ መዝጊያ ቀን ማስታወቂያዉ ከወጣበት 10ኛዉ ቀን ላይ 11፡35 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገኘዉ ዋጋ ማቅረቢያ ዋጋቸዉን ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል ዋና እና ኮፒዉን እንዲሁም ፋይናንሻሉን ዋና እና ኮፒዉን በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ ደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናስ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ማንኛዉም ተጫራች መጫረት የሚችለዉ በሚመለከታቸው የንግድ ስራ ፈቃድ /ስራ ዘርፍ/ ብቻ ነው።

11. ት/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅቶች ያሸነፊባቸዉን እቃዎች በራሳቸዉ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለባቸው። በተጨማሪም ት/ቤቱ ከገዙት እቃዎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ 20% የመጨመር ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ያሸነፊትን ጠቅላላ ዋጋ ዉል ከመፈረማቸው በፊት 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸኋል።

12. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ድርጅቶች የሚወዳደርባቸውን እቃዎች ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

13. ት/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡።

14. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰዉን ብር ከታወቀ በባንክ በደጃዝማች ኡመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም CPO 0.7% በማሰራት ከዋናዉ የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ሎት

ሎት 1

ሎት 2 

ሎት 3

ሎት 4

ሎት 5

ሎት 6

ሎት 7

ሎት 8

ሎት 9

ሎት 10

ብር

10,500

11,200

7,000

700.00

11,200

2,100

2,800

11,200

2,100

8,400

ማሳሰቢያ፡–

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቼክ ማስያስ ከዉድድር ዉጪ የሚደረግ መሆኑን እናሳስባለን።

የግዥ መመሪያውን አንድ ላይ በተጫራች መሞላት ያለባቸውን ክፍሎችን ሞልተዉ ማህተም ተደርጎ ተያይዞ መመለስ አለበት።

አድራሻ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አጣና ተራ ወረዳ 10 ጀርባ ወይም ሪንግ ሮድ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።

ስልክ ቁጥር 011-273-8632 / 011-280-4094

የደጃዝማች ዑመር ሰመተር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት