ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል


Reporter (Nov 01, 2026)

የጨረታ ቁጥር ELiG/07/2026

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ሎት

አይነት

መለያ

1

ሎት 1

የፋይል ማስቀመጫ ቁም ሳጥን

የቢሮ ፋይሎች ማስቀመጫ ቁም ሳጥን ግድግዳ ላይ ሚገጠም

2

ሎት 2

የመኪና ጎማ

የአውቶሞቢል እና ፒክአፕ

በጨረታው ለመሳተፍ፡–

1. ተጫራቾች ከላይ ከተገለፁት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ በሁሉም ወይም በተናጠል መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ ኢማ ስም በሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት መስቀል ፍላወር በሚገኘው የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት “ሆም ኦፍ ሚሊዮንስ” ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውስድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በዚሁ ቀን ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በኩባንያው የስልጠና አዳርሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።

7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 2077 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት

መስቀል ፍላወር ሆምስ ኦፍ ሚሊዮንስ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ

ስልክ 011 470 2077 / 011 557 0606


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *