Addis Zemen (Nov 03, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር የምተ ዐ1/2019
በማ/ኢ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገ/ህ/ሥራ ኃ.የተ. ዩኒየን በ2019 ዓ/ም ከጂቡቲ ወደብ እየቀረበ በዞኑ ዋና ከተማ በሳጃ ማዕከላዊ መጋዜን የሚከማቸውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ወረዳዎች በሚገኙ 19 ሽያጭ ጣቢያ መጋዘኖች ለማጓጓዝ በደረቅ ጭነት አገት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ባለንብቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የተፈለገው አገ/ት |
የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ |
|
1 |
አንድ |
ደረቅ ጭነት አገ/ት |
20,000.00 |
1. የዩኒየኑን ህገ–ደንብ የሚያከብርና ከማንኛውም ስነ ምግባር ችግር የፀዳ ፤
2.የተለያዩ የዘር ወቅት ሁኔታ፣ የጣቢያዎቹ ኮታ፣ የመጋዝን ጥበትና የመሳሰሉትን ችግሮች ታሳቢ በማድረግ የዞኑ ግብዓት ኮሚቴ የሚያስቀምጣቸውን ወቅታዊ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ለመስተናገድ ፍቃደኛ የሆነና የመተባበር ባህርይ ያለው፤
3. የአገ/ት ከፍያን በተመለከተ የጊዜ ገደብ እየሰጠ ተረጋግቶ ከሽያጭ ገቢ መቀበል የሚችል፣
4. በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተኢታ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN) ዋናና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታና የውል ማስከበሪያ የ20,000.00 ብር /CPO/ አሰርቶ ማቅረብ አለባቸው።
6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 ብር በመክፈል ወስደው በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በግልጽ በአማርኛ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት መጠየቂያውን ሙሉ በሙሉ በመሙላት በፖስታ በሚገባ አሽጎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው። የፈለጉትን ቦታ ብቻ መርጠው መሙላት አይቻልም።
7. በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
8. ዩኒየኑ ከማንኛውም ጨረታ አሸናፊ ጋር የራሱን አይሱዙ መኪና አሰማርቶ የማሠራት መብት አለው።
9. የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታ መክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን አያስተጓጎልም።
10 የጨረታ አሸናፊ ወዲያው የሚገለጽ ቢሆንም ጨረታው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህ/ሥራ ኮሚሽን ፀድቆ እስኪቀርብ በትዕግስት መጠበቅ አለበት።
11. በክልሉ ፀድቆ ሲቀርብ የጨረታ አሸናፊ ቀርቦ ውል ገብቶ ማጓጓዝ እንዲጀምር ጥሪ ይደረጋል።
12 ጨረታውን ያላሸነፉት ጨረታው ከፀደቀ ከ28 ቀናት በኋላ ሰነዶቻቸውንና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
13.በጨረታው ላይ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልግ ቅሬታውን ጨረታው በተከፈተ እስከ 3 ቀናት ውስጥ ብቻ ለየም ዞን ሕ/ሥራ ጽ/ቤትና ለዩኒየን ጽ/ቤት በጽሑፍ በማመልከቻ ማቅረብ ይችላል።
14. ከ3 ቀናት በኋላ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቀርብ የቅረታ አቀራረብ ተቀባይነት አይኖረውም፤
15. ዩኒየኑ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠሙት ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. መመዝገቢያ ጊዜ፦ ይህ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ይሆናል።
17. መመዝገቢያ ቦታ ፡– በሳጃ ከተማ ከአ አበባ ጂማ በሚሄደው አስፋልት ላይ 240 ኪ/ሜትር በየም ዞን ሕ/ሥራ ል/ጽ/ቤት ግብዓትና ግብይት ዳሬክቶሬት እና በፎፋ ለሚመዘገቡት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ሃሳብ ከፍል ዘወትር ሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ይሆናል፣
18.ዩኒየኑ ጨረታውን የሚሰርዝበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ለተጫራቾቹ ገንዘባቸውን ወድያው ይመልሳል።
ለበለጠ መረጃ 0910292780/0942356924/0913197219 ይደውሉ።
ቴሌግራም 0952198603 ኢሜይል yemtebaberunion@.com
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች
ሕ/ሥራ ኃ.የተ. ዩኒየን/ሳጃ/