Addis Zemen (Nov 03, 2026)
የመሬት ሊዝ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ/
ጨረታ ቁጥር 01/2019
በአብክመ በሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ የሚገኙ የንግድ እና የመኖሪያ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአልሚዎች በሊዝ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡-
- በአጣዬ ከተማ 02 ቀበሌ እስታዴየም ጀርባ እነ አባተ ፋንታይ ይኖሩበት የነበረው ያለው ቦታ የቦታ ምደባ መኖሪያ፣ የቦታ ስፋት 229.5 ካ.ሜ፤ የቦታ ደረጃ 2ኛ፤ የህንጻ ከፍታ G +0
- በአጣዬ ከተማ 02 ቀበሌ አስታዴየም ጀርባ እነ አባተ ፋንታይ ይኖሩበት የነበረው ያለው ቦታ የቦታ ምደባ መኖሪያ፤ የቦታ ስፋት 229.5 ካ.ሜ፣ የቦታ ደረጃ 2ኛ፤ የህንጻ ከፍታ G+0
- በአጣዬ ከተማ 02 ቀበሌ ፍርድ ቤቱ ፊትለፊትወይም ሃሙስ ገበያ መግቢያ በኩል የቦታ ምደባ ንግድ የቦታ ስፋት 339.15 ካ.ሜ፣ የቦታ ደረጃ 1ኛ፣ የህንጻ ከፍታ G+2
- በአጣዬ ከተማ 01 ቀበሌ ከዘነቡ አዘነ ግሮሰሪ ጀርባ የቦታ ምደባ ንግድ ፣ የቦታ ስፋት 278.33 ካ.ሜ ፤በቦታ ደረጃ 2ኛ፣ የህንጻ ከፍታ G+2
- በአጣዬ ከተማ 03 ቀበሌ እነ ወ/ሮ ጸሃይ ይመር ይኖሩበት የነበረው : በልዩ ጨረታ የቦታ ምደባ ንግድ የቦታ ስፋት 533.2 ኪ.ሜ፣ የቦታ ደረጃ ıኛ፣ የህንጻ ከፍታ G+4
- የጨረታ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሆኖ በቦታው በሊዝ መነሻ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚፈለግበትን ቅድመ ክፍያ መጠን ማሸነፉ እንደተገለጸለት ወዲያውኑ 20% እና ከዚያ በላይ ቅድሚያ ይከፈላል
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቀርበው ገንዘብ ወይም ሌላ የዋስትና ማረጋገጫ ሰነድ ከጠቅላላው ዋጋ ላይ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠው ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ አጣዬ ከተማ ኣስ/ገ/ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር ብቻ በመከፈል በአጣዬ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ የጨረታ ሰነዱ የሚመለሰው በዚሁ ጽ/ቤት ይሆናል።
- ተጫራቾች ቦታዎችን ተዘዋዉረዉ በአካል ማየትና መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ጊዜን በተመለከተ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚዘጋበት ቀን ጨረታው ከወጣበት በ10ኛ ቀን 11:00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው በተገኘበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ሲፈለጉ በስልክ ቁጥር 0336610688/ 0336610011 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ23/02/19 ዓ.ም እስከ 2/03/19 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ 11:30 ሰዓት አጣ/ከ/አስ/ መሬት ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ስዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-በኮድ አንድ ላይ በልዩ ጨረታ በተገለጸው ላይ የሚጫረት ተጫራች
- የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያለው ፣ የፀደቀ ፕሮፖዛል ያቀረበ ፣ከዞን የድጋፍ ደብዳቤ ያለው እና እንዲያለማ የከንቲባ ኮሚቴ ውሳኔ ያለው ባለ ኮኮብ ሆቴል መገንባት የሚችል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር
መሬት ጽ/ቤት