በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auctionet  ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

በመሆኑም፡–

1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት (ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et   ማያያዝ ይኖርበታል።

2. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE 03 አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

የዕቃ ግልጽ

እስከ 01/03/2019

02/03/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡– ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች| ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።

7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 -05-11-55 -11

አድራሻ፡– ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡– 011-470-85-03

አድራሻ፡– ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

በጉምሩክ ኮሚሽን አአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት