Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ባምዘማ/ሽ 18/2019
በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በ2018/19 ምርት ዘመን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያስመረተውን ምርጥ ዘርና የምግብ እህል በጨረታ አወዳድሮ ወደ ባሕር ዳር ወይም ወረታ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ዘርፍ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድና በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የተሸከርካሪዎች ዝርዝር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚጓጓዘው ምርጥ ዘርና የምግብ እህል ብዛት እንደየቦታው የሚለያይ ሆኖ ለአንድ ኩንታል የሚያጓጉዝበትን ዋጋ በመሙላት መቅረብ አለባቸው፡፡ ዝርዝር መጠኑ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት መጠን የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በማሸግ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 3/2019 ዓ.ም ለቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 78 74 49 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 16 ጉደር ዱቄት ፋብሪካ በስተጀርባ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች
ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት