በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የቢሮ ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የቢሮ ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሎት 1. ለፋርጣ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት የቢሮ ግንባታ፣ ሎት 2. ለአስተዳደር ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ሎጅስቲክ ግዥ (ምስር ክክ፣ አኩሪ አተር ክክ፣ የምግብ ዘይት፣ ሎት 3. ለባህልና ስፖርት ጽ/ቤት በስፖርት ምክር ቤት በጀት የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡፡

1. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን እና በወቅቱ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

4. ለግንባታው የሚሳተፉ የተቋራጮች ደረጃ 5 በላይ እና የግንባታ ፈቃድ ዘርፍ ለመስራታቸው በወቅቱ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለስፖርት ትጥቅ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለምግብ ዘይት ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለግንባታ፣ ምስር ክክ እና አኩሪ አተር ክክ 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ በሲፒኦ በባንከ ፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ስም እንዲሁም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በፖስታው አብሮ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ጨረታው የሚገመገመው በመደበኛው የክልል የግዥ የጨረታ መመሪያ መሰረት ሲሆን የግንባታ ጨረታው በተቀመጠው የአነስተኛ ግንባታ (ህንጻ) አጠቃላይ የውል ሁኔታ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

8. በጥቃቅን የተደራጁ ተወዳዳሪዎች የሚገመገሙት ልዩ ድጋፍ ሳይደረግ እንደ ማንኛውም ሌሎች ተጫራቾች እኩል ስለሚገመገሙ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በተጠየቀው አግባብ አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. አሸናፊው የሚለየው በጨረታ ሰነዱ የቀረበውን መነሻ በማድረግ ተገምግመው ከሚያልፉት ተጫራቾች መካከል በዋጋ ተነፃፅሮ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገው መላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ለግንባታ ጨረታ ተወዳዳሪዎች  የፋይናንሻል ዋጋ የሞሉበት የማወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ  ለየብቻ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በቀረበው የዋጋ መሙያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን እንዲሁም ለግንባታ (ቢል ኦፍ ኳንቲቲ) ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና ስምና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. አሸናፊው ድርጅት ከተለየ በኋላ ለእቃ አቅርቦትም ሆነ ለግንባታ ስራው የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና 10 በመቶ እና መ/ቤቱ ለሚከፍለው 30 በመቶ ቅድመ-ክፍያ ዋስትና በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ጋራንቲ (ሲፒኦ) ከህጋዊ ባንክ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለዕቃ አቅርቦት እስከ 10ኛው ቀን ለግንባታ እስከ 20ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከሚዘጋበት ከረፋዱ 3፡30 በኋላ የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የማይኖረው ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3፡45 ይከፈታል፡፡

14. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ባቀረበው የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ዝግ ፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆኑ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡

15. የጨረታ መገምገሚያ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተ ጊዜ አንስቶ ለ40 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ግምገማው ከተቀመጠው ጊዜ በላይ የሚፈጅ ከሆነ ተቋሙ ዕጩ ተጫረቾችን  የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበትን ተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

16. በሁሉም ሎት አሸናፊው እንደተለየ እና የቅሬታ ማስተናገጃ ጊዜው በተጠናቀቀ በአምስት ቀን ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል የሚያዝ ይሆናል፡፡ ለግንባታ ስራውም ቦታ ርክክቡም ውል በተያዘ በአምስት ቀናት ውስጥ ይፈጸማል፡፡

17. የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም የቦታ ርክክብ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ከተቋሙ ጋር በፍትህ በሚፀድቅ የውል ቀን  ይሆናል፡፡

18. የጨረታ ሠነድ የመሸጫ ለእቃዎች ዋጋ ብር 500 (አምስት  መቶ ብር) እና ለግንባታ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ ነው፡፡

19. ርክክቡ የሚፈፀመዉ የግንባታ ሥራው በሙያተኛ ተረጋግጦ ሲሆን የእቃ አቅርቦትን በተመለከተ በተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ይሆናል፡፡

20. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ያወጡትን ወጭ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ ይሆናል፡፡

21. በማስታወቂያው ያልተገለጹ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

22. ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደዉለዉ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *