Melekite Dire (Oct 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር አለ/ ሁ/ደ/ ት/ቤት ግ /ጨ/01/2019
በድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአሰሊሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019ዓ.ም. ለትምህርት ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ
- የፅህፈት መሳሪያዎችና
- የፅዳት እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት
ህጋዊና ብቃት ያላቸዉ የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
1.የጨረታ ሰነድ ክዚህ ቢታች በተራ ቁጥር ዘጠኝ በተጠቀሰዉ አድራሻችን መሰረት ለአንዱ በት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ ብቻ /200.00/ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛዉ ቀን ጠዋት 3፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአሰሊሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።ይህ ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።
3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ አካተዉ ማቅረብ ያለባቸዉ ሰነድ የሚከተሉት ናቸዉ፦ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ ና በዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ ፧ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገበ፤ በተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸዉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተገለፀዉ ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ሲፒኦ/ጥሬ ገንዘብ ያላስያዘ ቢኖር ሰነዱ ብቻ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ዋጋ የለዉም።
|
ሎት |
የእቃዎች መግለጫ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት አንድ |
አላቂ የቢሮ እቃ |
5000.00 |
|
ሎት ሁለት |
አላቂ የትምህርት እቃ |
|
|
ሎት ሶስት |
ከአንድ አመት በላይ አገልግሎት የሚሰጡ የቢሮ መገልገያ እቃዎች |
|
|
ሎት አምስት |
የጽዳት እቃዎች |
5000.00 |
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃዎች ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር በጨረታ መክፈቻ እለት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
7. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ በተጨማሪም ተጫራቾች አቅርቦቱን በራሳቸዉ ትራንስፖርት አግዘዉ በትምህርት ቤቱ አጥር ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ከተጠየቀዉ የእቃ መግለጫ ውጪ ቢቀርብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
8. ት/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ ተጠበቀ ነዉ።
9. ለማንኛዉም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰዉ አድራሻ ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡– ስልክ ቁጥር 0977858959/0939503410