አል-ዓፊያ አክሲዮን ማኅበር የ2019፣ 2020 እና 2021 የሂሳብ ዓመት የፋይናንስ መግለጫዎቹን እንዲመረምሩ ነፃ የውጭ ኦዲተሮችን ወይም የኦዲት ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ ይጋብዛል – test3.diretenders.com

አል-ዓፊያ አክሲዮን ማኅበር የ2019፣ 2020 እና 2021 የሂሳብ ዓመት የፋይናንስ መግለጫዎቹን እንዲመረምሩ ነፃ የውጭ ኦዲተሮችን ወይም የኦዲት ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ ይጋብዛል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የውጭ ኦዲተር ቅጥር ማስታወቂያ

አል-ዓፊያ አክሲዮን ማኅበር የ2019፣ 2020 እና 2021 የሂሳብ ዓመት የፋይናንስ መግለጫዎቹን በሙያቸው ብቃት እና ልምድ ያላቸው ነፃ የውጭ ኦዲተሮች ወይም የኦዲት ድርጅቶች በየተጠቀሱት ዓመታት በተናጠል እንዲመረምሩ እና የኦዲት ሪፖርቱን ለዳይሬክተሮች ቦርድ እና በየዓመቱ በሚከናወነው የባለ-አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዲያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።

የተወዳዳሪዎች መስፈርት፡-

  1. በፌዴራል ኦዲት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ወይም በሚመለከተው ባለሥልጣን የተሰጠ የኦዲት ሥራ ፈቃድ ያለው።
  2. የ2018 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ዋናውን እና ቅጂ ማቅረብ የሚችል።
  3. የቲን (TIN) ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
  4. በተመሳሳይ የኦዲት ሥራዎች ቢያንስ 5 ዓመት ሥራ ልምድ ያለው እና
  5. ከዚህ ቀደም የሠራቸውን ተመሳሳይ ሥራዎች ማስረጃ (Reference) ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

የመወዳደሪያ ሰነድ አቀራረብ

ተወዳዳሪዎች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በማኅበሩ ዋና ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

አድራሻ:-

አል-ዓፊያ አክሲዮን ማኅበር፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 7 ቤተል አደባባይ አጠገብ በሚገኘው ሣራ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር :- +251 989 79-25- 23/09 30- 48 36 13 ላይ ይደውሉ፡፡

ማሳሰቢያ:-

  • መስፈርቱን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ለቀጣይ ውድድር ይጠራሉ፡፡

የአል-ዓፊያ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *