የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን (ቧንቧ መገጣጠሚያ፣ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ፣ የጽህፈት መሳርያ፣ ብትን ጨርቅ፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የወንድ እና ሴት ጫማ፣ እና ልብስ ስፌት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን (ቧንቧ መገጣጠሚያ፣ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ፣ የጽህፈት መሳርያ፣ ብትን ጨርቅ፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የወንድ እና ሴት ጫማ፣ እና ልብስ ስፌት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር02/2019

የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም፡

  1.  ቧንቧ መገጣጠሚያ
  2. ባለ 3 እግር ተሸከርካሪ
  3. የጽህፈት መሳርያ
  4. ብትን ጨርቅ
  5. የተሰፉ ልብሶች
  6. የወንድ እና ሴት ጫማ
  7. ልብስ ስፌት

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል፡፡

  1.  በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2.  በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት / በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፣
  4. ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅርብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፓስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ውሃ/አዝ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም፡፡
  7.  ሰርፌስ ፓምፕ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያችሁን እና ቴክኒካል ሰነዳችሁን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማስገባት ይኖርባኋል፡፡
  8. በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠቱ 3፡00 ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ ድርጅቱ አይሸፍንም ፡፡
  10. ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል፡፡
  11. ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. የቧንቧናመገጣጠሚያእቃዎች፤ሸሚዝ እና ብትን ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፤ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጅ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጣችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን፡፡
  2. ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

 አድራሻ – ደ/ማ/ከ/ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587716840፣0587711058፣0587711520

ደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት