የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1. ጅኤስ ቧንቧ መገጣጠሚያ፣
  • ሎት 2. ኤች ዲፒ መገጣጠሚያ፣
  • ሎት 3. የቧንቧ መፍቻዎችና የስራ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 5. የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣
  • ሎት 6. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣
  • ሎት 7. ኤሌክትሪክ እቃዎች፣
  • ሎት 8. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 9. የዉሃ ጥራት ኬሚካል ሪኤጀንት፣
  •  ሎት 10. እስቴሽነሪ፣
  • ሎት 11. የደንብ ልብስ ጫማ እንዲሁም
  • ሎት 12. የኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  5. የግዥዉ መጠን ከብር 500‚000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች ከ1-6 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይዉላል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል፤ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10.  በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም፡፡
  11.  የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለስላቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች የማይመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (በጥሬ ገንዘብ) ለፍኖተሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/አገ/ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
  15. ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ም ድብ (ሎት) በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ፡፡
  16. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ ድርጅቱ ኃላፊነትን አይወስድም፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 13 87 /00 75 /09 23 42 61 23 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት