Addis Zemen (Nov 04, 2026)
የ3ኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ 11 ቦታዎችን የመኖሪያና የድርጅት ጠቅላላ የቦታው ስፋታቸው 2415 ካሬ ሜትር የሆነውን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃድኛ የሆኑ ተጫራቾች :-
1. የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ቦታው የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 30 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 30 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡
5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ24/02/2019 ዓ.ም እስከ 07/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 07/03/2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ08/03/2019 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ ከነ አባላት ስም ዝርዝር የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
10. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ :- በስልክ ቁጥሮች 0912 871 993 / 0931 969 182 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት