በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ፋይናንስ/ፕ/ጽ/ቤት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ፋይናንስ/ፕ/ጽ/ቤት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ፋይናንስ/ፕ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳ ስር ለሚገኙ ለሴክተር መ/ ቤቶች እና ታ/ማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በቀረቡ ዝርዝር መሰረት፡-

  1. ሎት1. እስቴሽነሪ ዕቃዎች ግዥ
  2. ሎት2. የሞተር ሳይክል ግዥ
  3. ሎት3. የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1.በሚወዳደሩት የንግድ ዘርፍ ለ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣

2.የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፣

3.የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ላት፣

4.የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ነች

5.የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፣

6.የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሐያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከበና ፀማይ ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በበና ፀማይ ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር (01) በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

7.ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ሎት 1 በ22ኛው ቀን /ሀያ ሁለተኛው/ ፣ ሎት 2 በ23ተኛው ቀን ፣ ሎት 3 በ24ተኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ከ4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9.ተጫራቾች ያሸነፉባቻውን ዕቃዎች እስከ በና ፀማይ ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ዐ4 ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10.ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ዕቃዎች ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ በበና ፀማይ ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መግባት ይኖርባቸዋል።

11.ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ያለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ሂደትን አያስተጓጉልም ውጤቱ ከተገለፀ ማየት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251916856290
በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ፋይናንስ / ፕ / ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *