Addis Zemen (Nov 04, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ/58/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የመያዣ አይነት/ ሞዴል |
የሽንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ |
ጨረታው የሚከናወንበት |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
|||||||||
|
1 |
አቶ ምህረት ፈረደ ታረቀኝ |
አቶ ምህረት ፈረደ ታረቀኝ |
እንጅባራ |
አአ-03-B37782 |
ቶዮታ ሀይሉክስ ድርብ ተግባር 2021 |
MROBA8CD4M0236614 |
1GD-5035113 |
11,880,000.00 |
ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም |
ከ 4:00 እስከ 5፡00 ሰዓት |
አማራ ባንክ አ.ማ ዋናዉ መ/ቤት |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት; በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ከፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤የመንጃ ፍቃድ፤ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፤ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፤ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
10. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
11. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል፡፡
አማራ ባንክ አ.ማህበር