2merkato.com (Nov 05, 2026)
የጨረታ መክፈቻ ቀን ማራዘሚያ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ-አምስት አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ጥቅምት 15፣ 2019 ዓ.ም በታተመው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ለወጡትና በመደብ ሀ እና ረ ላይ የተመለከቱት ጨረታዎች መዝጊያ ቀናት ለአስር ተከታታይ ቀናት የተራዘሙ መሆኑን እያሳወቅን፣ የነዚህና የምድብ ሐ፣ ሠ፡ እና ሸ መክፈቻ ቀናት ኅዳር 4፣ 2019 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የመክፈቻ ቀን ለተራዘመባቸው ምድባች የመወዳደሪያ ሰነድ ያስገቡ ድርጅቶች እንደፍላጎታቸው ባቀረቡት ሰነድ እና ናሙና ውድድሩን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣ መለወጥ፤ ማስተካከል፡ ወይንም ማሻሻል ለሚፈልጉት ማንኛውም የጨረታ ዶሴ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል፡፡፡
ምድብ ሀ፡- በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን እና በሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ት/ቤት ስልጠናቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የደረቅ ምግብ እና የባልትና ውጤቶች አቅርቦት፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ሐ፡- ድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን የሚገልፅ ሁለት የማስተዋወቂያ ሰሌዳዎች/DIGITAL SIGNAGE/ ሥራ እና ተከላ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ሠ፡- በባህርዳር የሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ለሚካሄደው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ከድርጅቱ የውሃ ሥርጭት መስመር ጋር የማገናኘት ሥራ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ረ፡- የድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አጋር ከሆኑ የመንግስት ጤና ተቋማት ጋር በጋራ እየተተገበረ ላለው የፕሮጀክት ዜሮ አገልግሎት የሚውሉ ስድስት/06/ የሞተር ሳይክሎች ግዢ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ፤
ምድብ ሸ፡- በደስታ መንደር መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል የሚገኙ እና በሰባት/07/ ምድቦች የተለዩ፣ አገልግሎት ላይ ውለው የሚወገዱ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና የመኪና ጎማዎች ሽያጭ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ፡፡
ተጫራቾች ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው ምድቦች የተዘጋጁትን ሰነዶች በየምድቦቹ አንፃር የተገለፀውን የሰነድ ክፍያ በመፈፀም ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ምድቦች ጨረታ እስከ ኅዳር 4፣ 2019ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ምድቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46-የውስጥ መስመሮች፡ 139/182፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹ ላይ በተገለፁት የስልክ ቁጥሮች ደውለው የሚያስፈልጋቸውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6adf262a0a538a33e5000001