የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን የዳልጋ ከብት ቀንድ እና የስጋና አጥንት መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን የዳልጋ ከብት ቀንድ እና የስጋና አጥንት መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 05, 2026)

በድጋሚ የወጣ የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን የዳልጋ ከብት ቀንድ እና የስጋና አጥንት መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

  • ለስጋና አጥንት መኖ በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት፡፡
  • ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ፣ማክሰኞ እና ሐሙስ) ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
  • አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
  • የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ለስጋና አጥንት መኖ ህዳር 02 ቀን 2019 ዓ.ም እና ለዳልጋ ከብት ቀንድ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በ8868/0114163978 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *