Addis Zemen (Nov 06, 2026)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የስፖርት ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ጨረታ፡
- ሎት 1. የጂምናዚየም ማሽኖች እና ቁሳቁሶች ግዢ ……..200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘቡና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ሠነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ከላይ በተቀመጠው አግባብ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ሰነድ የሚመልሱበት በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በቢሮ ይከፈታል።
9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶና ኦርጅናሉ ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብና ሌሎችንም ዕቃዎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት ዋጋቸውን በአግባቡ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ጂም ማቴሪያሎቹ የሚቀርበት ዋጋዎች በተናጠል ሳይሆን በሎት/በጥቅል ዋጋ/በፉል ሴት ነው
12. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በጨረታ ሠነድ ክፍል 4, 6 እና 9 የተቀመጡ ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሞልተው ያልቀረቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
13. አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስረከቢያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
15. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገቢያ በሚቀርብበት ዕቃ/ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት ዕቃ ከገቢያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እያንዳንዱ ምርት ዕቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከቢሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
16. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።
17. መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ አዲሱ የክፍስ ከተማ ህንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 የአራዳ ክ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
ስልክ ቁጥር 09 00 019 739
የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን