በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 06, 2026)

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች አላቂ የትምህርት እቃዎች ሲፒኦ 20,000
  • ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ሲፒኦ 25,000
  • ሎት 3 የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት ሲፒኦ 25,000
  • ሎት 4 ለተለያዩ ጥገና የሚውሉ አላቂ እቃዎች ሲፒኦ 5,000
  • ሎት 5 ቋሚ መገልገያ እቃዎችና መሳሪያዎች ሲፒኦ 20,000
  • ሎት 6 የኮምፒውተር ፎቶ ኮፒ ማባዣ ጥገናና ሌሎች ስራዎች ሲፒአ 2,000
  • ሎት 7 ህትመት ሲፒኦ 5,000

በዚህ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት እቃዎች ላይ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

6. አምራች ሆነው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው

7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1 -7 የሚሰላ ብር 2% በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

8. የጨረታው ሙሉ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቀስተ ደመና የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 (ወረዳት ፋይናንስ ቢሮ) በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።

9, ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው የሚያበቃው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይሆናል።

11. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ ወዲያውኑ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።

12. የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማስከበሪያ ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የውል ማስከበሪያ ሳያስይዙ ውል መዋዋል አይቻልም።

13. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት ቀን በፊት ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም።

14. የጨረታው ሙሉ ሰነድ ሳይገነጠል መመለስ አለበት። ሙሉ ሰነድ ያላስገባ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።

15. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

16. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– መሳለሚያ ወረዳ 9 ከሞቢል ከፍ ብሎ እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ፡– 011 21 13 50 68

ቀስተደመና ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት