Addis Zemen (Nov 06, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019
የሲዳማ ብ//ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል.
- ሎት 1 ኤሌክትሮክስ
- ሎት 2 ፈርኒቸር
- ሎት 3 ተሽከርከሪ (ሞተር ሳይክል)
- ሎት 4 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 5 የፅዳት ዕቃዎች
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡
1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና TIN ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሁለት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 11ኛው ቀን ከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ እና የሞተር ሳይክል የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተብሎ ተለይቶ ኦሪጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባቸሁ።
5. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ለ30 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው።
6. ከላይ የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ይታሸግና በ6፡30 ይከፈታል።
8. በዕለቱ የኤሌክትሮኒክስ እና የተሸከርካሪ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ይሆናል።
9. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀን ቅዳሜና ዕሁድን ጨምሮ ነው።
10. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በሚለው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል።
11. የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በሲ/ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጄንሲ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000351753707 ገቢ በማድረግ በኤጀንሲው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል።
12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ፡-
- ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሀሣብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ የቀረበ ተጨማሪ ሰነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል።
- በመወዳደሪያ ሠነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሀሣብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የማወዳደሪያ ሃሣብ ይሰረዛል።
- አጠቃላይ የዕቃው ዝርዝርና ሲፒኦ ማስያዥያና ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
- ጨረታው ሰነድ ላይ ከጠቀመጠው እሰፔክ ውጪ ተጨማሪ አስፔክ በአስክሪፕቶ መጻፍ አይፈቀድም ይህ ሆኖ ቢገኝ ግን ከውድድሩ ውጪ የምናደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
አድራሻ-፡ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 221 7860
መጠየቅ ይችላሉ።
የሲዳማ ብ//ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ