Addis Zemen (Nov 06, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ /ደሴ ማረሚያ ቤት/ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል አቅርቦት ውል ወስዶ መግዛት ይፈልጋል፡-
1. የምግብ እህል፡- ቀይ ማሽላ፣ በቆሎ፣ አገሬ ነጭ ማሽላ
2. ቅመማ ቅመም፣ የወጥ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት፣ ዝቃቅቤ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ነጭ አዝሙድ እና የመሣሰሉት
3. ሸቀጣ ሸቀጥ፡- የልብስ ሣሙና፣ የእቃ ማጠቢያ ሣሙና /አጃክስ/፣ እርሾ፣ መኮረኒ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ የእቃ ማጠቢያ ሽቦ፣ ስኳርና የመሣሰሉት፣ እና ዛላ በርበሬ ከታህሳስ 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ማቅረብ የሚችሉ ነጋዴዎችን እንደየ ሁኔታው ለአንድ አመት በማጫረት ከአሸናፊው ጋር ውል ለመያዝ ይፈልጋል።
ስለዚህ፡-
1. ለሁሉም የስራ ዓይነት በየዘርፋ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ለሁሉም የስራ ዓይነት በየዘርፋ የግዥው መጠን ብር 200000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ጨረታው በሚከፈትበት እለት የሚጫረቱበትን የእህል ዓይነትና ዛላ በርበሬ ናሙና ከ50 ግራም ያላነሰ ይዞ መቅረብ አለበት ናሙና ማቅረብ ያልቻለ ተጫራች በጨረታው መጫረት አይችልም።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ብዛት የሞላትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር በአንድ ዓመት አባዝተው የዚያን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና / በአማርኛ የተተረጐመ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ/ ማስያዝ ይኖርበታል።
5. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ የሁሉም የስራ ዘርፍ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ከደሴ ማረ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ብቻ / ከፍሎ መውሰድ ይችላል።
6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሰነድ የሚገዛበት ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በደቡብ ወሎ ደሴ ማረሚያ ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታ ሰነዱና መረጃው የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይሆናል።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 4:30 ታሽጐ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀናት ከቀኑ 4፡30 ታሽጐ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
9. የጨረታው አሸናፊ በአሸነፉት መሰረት ውል ባይወስዱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል። አሽናፊ ከሆኑ በኋላ ያሸነፋበትን እቃ ማረ/ቤቱ ድረስ በራሱ ወጭ ያስረክባል።
10. አንዱ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላው ማቅረብ የለበትም።
11. አቅርቦቱን በተመለከተ ከወጥ ሽንኩርት በስተቀር ማረ/ቤቱ በሚፈልገው መጠንና ልክ መሰረት ወር ከመግባቱ በፊት ከ25-30 ቀን ድረስ የወሩን የምግብ ፍጆታ አጠቃሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
12. የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% የአንድ አመት ጠቅላላ ዋጋ የሚያሲዝ ሲሆን ተጫራቾች ማብራሪያ የሚፈልግ ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 6516 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
13. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ለሚያደርጉት ግብይት ህጋዊ የሆነ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለበት።
14. ለታራሚዎች በአማካይ በየወሩ የሚቀርብ የምግብ እህሎች፣ ቅማማ ቅመም፣ ወዘተ…ብዛት በአማካይ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡።
15. ግዣችን ከሃያ ሺህ ብር በላይ ስለሚሆን ቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑን እናሳስባለን።
16. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች
መምሪያ /ደሴ ማረሚያ ቤት/