በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንገድ ቅዬሳ መሳሪያ/ማሽን (ሎት 1)፣ የድሮን ካሜራ እና ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 2)፣ የብሎኬት ማምረቻ ማሽን (ሎት 3) እና ሞተር ሳይክል (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንገድ ቅዬሳ መሳሪያ/ማሽን (ሎት 1)፣ የድሮን ካሜራ እና ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 2)፣ የብሎኬት ማምረቻ ማሽን (ሎት 3) እና ሞተር ሳይክል (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት

  • የመንገድ ቅዬሳ መሳሪያ/ማሽን፣
  • ለኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤት የብሎኬትማምረቻ ማሽን፣
  • ለመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ለቀረጻ የሚሆን የድሮን ካሜራ እና
  •  ለፖሊስ ጽ/ት የእጀባ ትራፊክ ሞተር ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. ሎት አንድ የመንገድ ቅዬሳ መሳሪያ/ማሽን ግዥ ጨረታ
  2. ሎት ሁለት ኤሌክትሮኒክስ እና ለቀረጻ የሚሆን የድሮን ካሜራ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
  3. ሎት ሶስት የብሎኬት ማምረቻ ማሽን ግዥ ጨረታ
  4. ሎት አራት የሞተር ሳይክል ግዥ ጨረታ

በዚህም መሠረት ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፤
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል፤
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO/ ያለው/ላት፣
  6. ተጨማሪ እሴት ታክስ  (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ነች፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር በጥሬ ብር ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በመሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ስም በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጅት በጥንቃቄ በታሸገ በሁለት ጥ ፖስታዎች ለየብቻው በማዘጋጀት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ እንደተመለከተው ለሚጫረቱት ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በ15ኛው ቀን ሎት አንድ በ3፡ዐዐ ሰዓት ታሸን 3፡30 ላይ ይከፈታል ሎት ሁለት በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ላይ ይከፈታል ሎት ሶስት በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ላይ ይከፈታል እና ሎት አራት በ9፡30 ሰዓት ታሽጎ10:00 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  11. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ዕቃ ወይም ንብረት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን፣ ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

ማሳሰቢያ

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ፡፡

የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ /ቤት