በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁ 0003/19

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ በ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡–

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቶች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 6 ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 በግልጽ ይከፈታል፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

6. ተጫራቾች ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡–

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ባለስልጣን

ቢሮ ቁጥር 6

የስልክ ቁጥር፡– 0942 279 841

በድሬዳዋ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ሎጅስቲክ ኤጀንሲ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *