የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አራዳ የካ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ለሚኩራ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አራዳ የካ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ለሚኩራ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Lessan (Nov 07, 2026)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የ9ኛ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አራዳ የካ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ለሚኩራ እና ቦሌ  ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በ addislandfarm.gov.et:  (https://addislandfarm.gov.et/land-auction)  በኦን ላይን በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 30/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።

2. ለጨረታ የወጡ ቦታዎችን በሊዝ ለመጫራት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1.1. ተጫራቹ ጨረታዉን መሳተፍ የሚፈልገው በግል ከሆነ የጨረታ ሰነድ ግዥ የሚፈጽመው በፋይዳ መታወቂያ ቁጥር ባለው ባለ አስራ ስድስት አሃዝ የካርድ ቁጥር (FAN) ብቻ በመጠቀም ማመልከት ይጠበቅባቸዋል።

1.2. ተጫራቹ ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልገው ህጋዊ ሰዉነት ባለው ማህበር ፣ አክሲዮን ወይም ድርጅት ከሆነ የጨረታ ሰነድ ግዥ የሚፈጽመው በማህበሩ ፣ በአክሲዮኑ ወይም በድርጅቱ ስም በተከፈተው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ብቻ በመጠቀም ማመልከት ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች ቦታውን በሲስተሙ ላይ በተቀመጠው google map አቅጣጫ ጠቋሚ (location) መሰረት በአካል መመልክት ይችላሉ። በተጨማሪ በ30/02/19 ዓ.ም ፣ 03/03/19 ዓ.ም እና በዐ7/03/19 ዓ.ም ጠዋት ከ3፡ዐዐ ሰዓት – 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት 8፡00 ሰዓት – 11፡30 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

4, አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘዉን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ወይም በድህረ ገጹ ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትዎርክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር መ/ቤቱ አይጠየቅም።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO) ብቻ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በመፃፍ ህዳር 11/2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በፖስታ አሸገው ሲያቀርቡ በፖስታው ላይ የሚጻፈው የጨረታ ቁጥርና የቦታ ኮድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው የቦታ ኮድና የጨረታ ቁጥር ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች ለአንድ ካሬ ሜትር የሚሰጡትን ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተገለጸው ድረ ገጽ በመግባት በተዘጋጀው የዋጋ መስጫና የቅድመ ክፍያ መጠን በፐርሰንት በቀጥታ መሙላት ይኖርባቸዋል። አሞላሉን በተመለከተ በዚሁ ደህረ ገጽ ላይ በተያያዘው አጭር ቪዲዮ በመታገዝ መሞላት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹ ደጋፊ ሰነዶች ጥራቱን በጠበቀ ስካነር ስካን በማድረግ ከሲስተሙ ባለው የመጫኛ ቦታ ላይ መጫን (Upload) ማድረግ ይኖርባቸዋል ።

8.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO) ከፊትና ከኃላ

8.2 የተጫራቹ ፋይዳ መታወቂያ

8,3 የቴሌ ብር ደረሰኝ

8.4 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ደብዳቤ

8.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ

8.6 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት

8.7 ጨረታውን የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸዉ።

8.8 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. የጨረታ አሸናፊዎች ጊዚያዊ ውጤት ህዳር 17/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ለመሬት ሊዝ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሲስተም በኦንላይን ይፋ ይሆናል። ከጊዚያዊ ውጤት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ ጊዚያዊ ውጤቱ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በሲስተሙ በተዘጋጀው ቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ማቅረብ ይችላሉ።

10. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ከወጡት ውጭ ያሉ በንግድ ባንክ ፣ ዳሽን፣ አብሲኒያ እና አዋሽ ባንክ የተሰሩ ሲፒኦዎች በቢሮ በኩል ወደ ባንኮቹ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሰሩ እና ከላይ ከተጠቀሱት ባንኮች ውጭ ያሉ ተጫራቾች የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።

11. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መስፍርት ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ በተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

12, መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡–

Website: addislandfarm.gov.et  : (https://addislandfarm.gov.et/land-auction)t.me/addisland 

Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau መረጃ ማግኘት ይቻላል።

@aa.land.administrator  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *