Addis Zemen (Nov 07, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ቅጽ opm-0005
- የጨረታ ዙር 1ኛ ዙር /2019 ዓ.ም
- የጨረታው ዓይነት መደበኛ ጨረታ ቁጥር 1/2019
- የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ–ሠ በተዘረዘረው መሰረት እንዲሁም በደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 በሊዝ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2005 ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎቶች የሚውል ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
- ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቦታ በከተማ አስተዳደሩ ፕላን ክልል ውስጥ የሚገኝ ባለ 215 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ ı(አንድ) ባለ 225 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1(አንድ) ባለ 235 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1(አንድ) ባለ 240 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1 (አንድ )ባለ 275 ካሬ ሜትር ሽንሻኖ 1(አንድ) ቦታ ጠቅላላ ድምር 5 (አምስት) የመኖሪያ ቦታ ድምር 1190 ካሬ ሜትር ለጨረታ ተዘጋጅቷል።
- ለድርጅት አገልግሎት የሚውል ቦታ ከተማ አስተዳደሩ ፕላን ክልል ውስጥ የሚገኝ ባለ 310.63 ካሬ ሜትር 1(አንድ) ቦታ ባለ 250 ካሬ ሜትር ባለ 218.5 ካሬ ሜትር 1(አንድ) ባለ 227.71 ካሬ ሜትር 1(አንድ) ባለ 360 ካሬ ሜትር 1 (አንድ) በጠቅላላ (አምስት) የድርጅት ወይም የንግድ ቦታዎች በጠቅላላ ድምር 1366.84 ካ.ሜ በጠቅላላ መኖሪያ + ንግድ = 2556.84 ካ.ሜ ለጨረታ ተዘጋጅቷል።
- ማንኛውም የጨረታው አሸናፊ የሆነ አካል ያሸነፈበትን ዋጋ ቅድመ ከፍያ ከ10% ማነስ የለበትም
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሲያሥገባ 5% ሲፒኦ በወረኢሉ ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ የከፈሉበትን ኦሪጅናሉን አያይዘው ማስገባት አለባቸው ከዚህ ውጭ ተቀባይነት የለውም
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት እና የማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በኮሚኒኬሽን ፌስ ቡክ ድረ ገጽ ወይም ሳይት በአየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ ጨረታው በአስረኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 11፡00 ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3፡00 በወ/ከ/አስ/02 ቀበሌ አዲሱ ህንጻ ግቢ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ አስፈጻሚ ኮሚቴው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን በወረኢሉ ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 18 በመገኘት የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ለመኖሪያም ለንግድም 500 /አምስት መቶ/ ብር በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወረኢሉ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ፌስቡክ ድረ ገጽ ዌብ ሳይት ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች የመኖሪያም ይሁን የንግድ ቤት ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች በተመሳሳይ የቦታ ኮድ ውጭ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ኮድ መግዛት ይችላሉ።
- የተጫራቾች የመገምገሚያ መስፈርት በሰነዱ ላይ የተገለጸ መሆኑን እናሳውቃለን ።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የጨረታ አስፈጻሚዎች ስ.ቁ 09 38 84 39 91 / 09 33 51 83 58/ 09 15 63 47 90 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል
የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቡድን