Melekite Dire (Nov 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የመቁ፦ 102169
ቀን 10/02/2019
በፍ/ባለመብት አቶ ኢብራሂም ኡስማን አሊ እና በፍ ባለዕዳ አቶ አወድ ኡስማን አሊ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 100389 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ተበሌ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር 3833 በቤት ቁጥር 4056 የሆነና ስፋቱ 255 ካ/ሜ የሆኖ በሟች ወ/ሮ ፋጡማ ፋራህ የተመዘገበ ቤት በመነሻ ግምት ብር 3,065,661 ሶስት ሚሊዮን ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ ብር በሆነ ዋጋ በሃራጅ ሽያጭ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ታህሳስ 3 ቀን 2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡10 ድረስ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን
ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡15 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመገቡ ታዟል
የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ ቀሪውን 1/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ወይም በሞዴል 85 በፍጹቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው። ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘ ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር 4ኛ ችሎት