Addis Zemen (Nov 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ግብአቶችን በጨረታ መግዛት
- ሎት1 የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 2 የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት3 ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት4 ህትመቶች
- ሎት 5 መድኃኒቶች፣ ሪኤጀንቶች እና የሕክምና እና የላቦራቶሪ እቃዎች
- ሎት6 የፅዳት ዕቃዎች ሎትን ጥገና እና
- አገልግሎት (የኮምፒውተርና ፕሪንተር የላውንደሪ ማሽን የፎቶ ኮፒ ማሽን እና
- የጀነሬተር ሰርቪስ እንዲሁም የጭነት አገልግሎት ለአንድ አመት የሚቆይ/
በግልጽ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፋይ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱ በሎት የማይመለስ ብር/200 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 413 መግዛት ይቻላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ማለትም ለቢሮ ዕቃዎች፣ ለፅዳት ዕቃዎች ለቋሚ እቃዎች ለመድኃኒት ፤ ሪኤጀንት እና የሕክምና ዕቃዎች 3,500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጂናልና ኮፒውን ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ኛው ቀን ድረስ በጤና ጣቢያው የግዢ ቢሮ ቁጥር 410 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- ሲፒኦ (CPO) የሚያያዘው ኮፒው ላይ መሆን አለበት።
- አሸናፊው የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- ኦርጅናል ፖስታዎችን በጨረታ መክፈቻ መወዳደር ወቅት የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ይሆናል።
- ጨረታው ለ10 የሥራ ቀን ከቆየ በኋላ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ዕለት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ፡– በቂርቆስ ክ/ከተማ ሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ ግዢ ክፍል ልዩ ቦታው ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ አጠገብ በስልክ ቁጥር 0114706040 መደወል ይቻላል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ