የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የጽህፈት መሣሪያ ፣ የጽዳት ዕቃ ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ የህንፃ መሣሪያ ፣ የስፖርት ዕቃ ፣ ደንብ ልብስ እና ደንብ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የጽህፈት መሣሪያ ፣ የጽዳት ዕቃ ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ የህንፃ መሣሪያ ፣ የስፖርት ዕቃ ፣ ደንብ ልብስ እና ደንብ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 12, 2026)

ሀገር አቀፍ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ፣

ቁጥር፡- ሐ/ኢ/ክ/ጨ3 -292/19ዓ.ም

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሀረጎ የማማከር የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ

  •  ሎት1 የጽህፈት መሣሪያ ፣
  • ሎት 2 የጽዳት ዕቃ ፣
  • ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣
  • ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ ፣
  • ሎት 5 የስፖርት ዕቃ ፣
  • ሎት 6 ደንብ ልብስ እና
  • ሎት 7 ደንብ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
  3. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 500,000.00 አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1–3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸው እቃዎች በባለሙያ ማስፈ ተሸና ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  7. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመከፈል በኢንተርፕራይዙ ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 002 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ
    • ለሎት 1 ብር 10,494(አስር ሺህ አራት መቶ ዘጠና አራት ብር ብቻ)፣
    • ለሎት 2 ብር 2844(ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አራት ብር ብቻ) ፣
    • ለሎት 3 ብር 4800(አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር ብቻ) ፣
    • ለሎት 4 ብር 2386(ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ብር ብቻ) ፣
    •  ለሎት 5 ብር 2403(ሁለት ሺህ አራት መቶ ሶስት ብር ብቻ)፣
    • ለሎት 6 ብር 1871(አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አንድ ብር ብቻ)፣
    • ሎት 7 ብር 1160 (አንድ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር ብቻ)በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11.  ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት/በጥቅል/ ጠቅላላ ድምር ነው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ መም/ትም/ኮሌጅ ሀርጎ የማማከር የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ በግዥ፣ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 002 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከ03/03/2019 ዓ/ም እስከ 12/03/2019ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዝ በግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 02 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመግኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠ/ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ እንድሁም ከፍት ያልተሞላ እቃ ካለ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  16. የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተቀመጡ ሳምፐሎች ስላሉ ሳምፕሉን ይመልከቱ፡፡
  17. ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ ሆየተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምግማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡-

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሀረጎ የማማከር

የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተር ፕራይዝ