Addis Zemen (Nov 13, 2026)
በድጋሚ የወጣ የሒሳብ ባለሙያ ጨረታ ማስታወቂያ
የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት / ሥራ ማህበር ከሐምሌ 01/2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ድረስ ያለውን የገቢ ደረሰኞች 593 ፓዶች (አምስት መቶ ዘጠና ሶስት) ፓዶች እና የወጭ ደረሰኞች 9 ፓዶች (ዘጠኝ) ፓዶች በድምሩ 602 ፓዶች (ስድስት መቶ ሁለት) ፓዶችን ሒሳብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ባለሙያዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- የታደሰ የሒሳብ ስራ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
- ቫት ከፋይ የሆነች እና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- የሒሳብ መሞከሪያ /trial balance/ ፣ የገቢ እና የወጭ /Income Statement/ ፣ የሀብት እና እዳ መግለጫ /Balance Sheet/ ሰርቶ በመጨረሻም የተገኘውን ግኝት በተጨባጭ ማስረጃ በማያያዝ የሚያቀርብ/ የምታቀርብ
- ሒሳቡ ካለቀ በኋላ ለኦዲተሮች የሰራውን ስራ ማስረዳት የሚችል/የምትችል
- በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ ዋጋችሁን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ለተከታታይ 10 ቀናት ማለትም ከ01/03/2019 ዓ.ም – 10/03/2019 ዓ.ም ድረስ በስራ ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
- ጨረታው የሚያበቃበት በ11/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ቦሌ ሚካኤል ኮንደሚኒየም ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ – 0911 418 022 / 0934 596 498 ይደውሉ።
የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት ሥራ ማህበር